በሰሜን ሸዋ ዞን የሰፈነው ሰላም በኅብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናከሮ መቀጠሉ ተገለጸ።

20

ባሕር ዳር: ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ የመንግሥት ሠራተኞች የተሳተፉበት የውይይት መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ ተካሄዷል። በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ እንደገለጹት፤ የሰላም አማራጭን ባለመቀበል በጥፋት መንገድ ለመቀጠል እየሞከረ ያለው የጥፋት ቡድን በኅብረተሰቡ ተሳትፎና በመንግሥት የፀጥታ ኀይሎች እየተመታ ነው።

በዞኑ የሰፈነው ሰላም በኅብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸው፤ የመንግሥት ሠራተኞች ሙሉ ጊዜያቸውን ሕዝብና መንግሥትን በማገልገል በጥፋት ቡድኑ ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ ከመደገፍ ባሻገር ተላላኪዎችን ማጋለጥ እንዳለባቸው ተናግረዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ መካሻ ዓለማየሁ በበኩላቸው፤ ችግሮችን በውይይት ለመፍታት መንግስት ትናንትም ዛሬም ቁርጠኛ አቋም እንዳለው ተናግረዋል።

ሆኖም የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ወደጎን በመተው የጥፋት መንገድ የተከተለው ቡድን እንደማይሳካለት ገልጸዋል። በመንግሥት የተጀመረው ሕግ የማስከበር ተግባር ተጠናከሮ እንደሚቀጥል አመልክተው፤ የመንግሥት ሠራተኞች የጥፋት ኀይሎችን አጋልጠው ለሕግ እንዲሰጡ አሳስበዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የሕዝብ ተሳትፎና የፖለቲካ አደረጃጀት አማካሪ ሰለሞን ጌታቸው፤ ውይይቱ ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ በእውነታ ላይ ተመስርቶ የሕዝብ ተሳትፎን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ተናግረዋል። በውይይት መድረኩ በየደረጃው የሚገኙ አመራር አባላትና የመንግሥት ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበክልሉ የተከሰተው ሰላምን የሚያውክ እንቅስቃሴ የአማራን ሕዝብ የማይመጥን እና ሊታረም የሚገባው አካሄድ መኾኑን የዳባት ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
Next article“የሕዝብን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በትኩረት እየተሠራ ነው ” አቶ እንድሪስ አብዱ