ሰላምን ሊያስከብር የሚችለው የሰላሙ ባለቤት ማኅበረሰቡ እንደኾነ የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ገለጸ።

42

ደሴ: ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት በኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከመንግሥት ሠራተኞች ጋር የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ በከተማው ሰላምን የሚያረጋግጡ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ያሉት በብልጽግና ፓርቲ የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሙልጌታ አቢ ናቸው። ሰላምን ሊያስከብር የሚችለው እራሱ የሰላሙ ባለቤት ማኅበረሰቡ ነው ብለዋል። ኀላፊው “እኔ ለከተማየ ሰላም አስተዋጽኦ አለኝ በማለት ሁሉም ለሰላም ዘብ መቆም አለበት” ነው ያሉት።

ሰው የሰላምን ዋጋ እኩል አይረዳም ያሉት አቶ ሙልጌታ ሰላምን የሚረዳው ሲያጣው ነው ብለዋል፡፡ ሰላምን ለማረጋገጥም ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የመንግሥት ሠራተኞች ሰላም ለመንግሥት ሠራተኛው የህልውና ጉዳይ ነው ብለው በየአካባቢያቸው ያለውን ሰላም ለማጽናት መረባረብ እንደሚረባረቡ ነው የተናገሩት፡፡

በውይይቱ ላይ የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች እና የሁሉም የመንግሥት ተቋማት ባለሙያዎች እየተሳተፋ ነው።

ዘጋቢ፡- አበሻ አንለይ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የተዋረድ ምክር ቤቶች ሕግ እና አሠራሮች እንዲከበሩና ሰላም እንዲሰፍን አሥፈጻሚውን አካል ክትትል እና ቁጥጥር ማድረግ ይገባቸዋል” ደሴ ጥላሁን (ዶ.ር)
Next articleየሕዝቡን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ታስቦ በመሠራቱ በክልሉ የተሻለ ምርት እንደሚገኝ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ፡፡