በርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የተመራ የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የተካተቱበት ልዑክ በደቡብ ወሎ ዞን ጃማ ወረዳ የሰብል ጉብኝት አካሄደ።

122

ባሕር ዳር: ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በአማራ ክልል ደረ የገበሬ በዓል በደቡብ ወሎ ዞን በጃማ ወረዳ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተው ባደረጉት የሰብል ጉብኝት ተከብሯል።

በሰብል ጉብኝቱ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ጉብኝቱ በጃማ ወረዳ 018 ቀበሌ 628 ሄክታር ሽፋን ያለው ቆጨም የስንዴ ኩታገጠም ልማት መኾኑን ከደቡብ ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣናን ለአፍሪካ ብልጽግና ሊፈጥር በሚችል መልኩ ሀገራት ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
Next article“ከሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ጋር በጋራ ሥንሠራ ለኅብረተሰቡ ፈጣን መረጃ ለመስጠት ያስችለናል” የአሚኮ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ሙሉቀን ሰጥዬ