የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የብድር ዕዳ በቦንድ ሽያጭ እንዲከፈል የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ።

72

ባሕር ዳር: ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባው የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

አዋጁ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወሰዱትን ብድር መመለስ ባለመቻላቸው ዕዳውን መንግሥት ተረክቦ በቦንድ ሽያጭ እንዲከፍል የሚያስችል ነው።

ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሳይሰበሰብ የቀረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር 845 ቢሊዮን 316 ሚሊዮን 570 ሺህ ብር እንደኾነ ተገልጿል፡፡

ባንኩ በመንግሥት ተፈቀደለት 4 ቢሊዮን ብር ብቻ በመኾኑ በገበያው ውስጥ ያለውን ድርሻ ለማስቀጠል ፈታኝ አድጎታል ነው የተባለው፡፡

በመኾኑም የድርጅቶቹ ዕዳ በቦንድ ሽያጭ እንዲከፈል የ900 ቢሊዮን ብር የቦንድ ሽያጭ እንዲፈቀድ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የ’World Without Hunger’ ጉባኤ ተሳታፊዎችን እንኳን ወደ አፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና በሰለም መጣችሁ እላለሁ።
Next articleየአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣናን ለአፍሪካ ብልጽግና ሊፈጥር በሚችል መልኩ ሀገራት ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡