“የ’World Without Hunger’ ጉባኤ ተሳታፊዎችን እንኳን ወደ አፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና በሰለም መጣችሁ እላለሁ።

34

አለምአቀፍ መሪዎችን፣ ባለሞያዎችን እና የጉዳዩ ተቆርቋሪዎችን በአንድ ላይ በማምጣት እንዲወያዩ በማድረግ የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ።

በኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ዓመታት በግብርና ሽግግር እና ምርታማነት ላይ በማተኮር የሠራነው ሥራ የታረሰ መሬታችን እጥፍ በማድረስ ከፍ ያለ እሴት ባላቸው የኢንደስትሪ አዝርዕት ምርት ላይ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች አስገኝቷል።

በሚቀጥሉት ቀናት የጉባኤው ውይይቶች የጋራ ግቦቻችንን ስኬት የሚያፋጥኑ ታላላቅ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ እተማመናለሁ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

Previous article“በ2017 በጀት ዓመት ከ5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የፍራፍሬ ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል” የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ
Next articleየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የብድር ዕዳ በቦንድ ሽያጭ እንዲከፈል የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ አፀደቀ።