“ከርሃብ ነጻ የኾነ ዓለም መፍጠር” በሚል መሪ መልዕክት ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

54

አዲስ አበባ: ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ከርሃብ ነጻ የኾነ ዓለም መፍጠር” በሚል መሪ መልዕክት ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ሙሳ ፋቂ ሙሐመት እና የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጀነራል ገርድ ሙለር ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት፣ ምሁራን፣ ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።

ጉባኤው እስከ ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

ዘጋቢ፡- ቴዎድሮስ ደሴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ እና ጀርመን በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ እና በግብርና ምርቶች ላይ በጋራ ለመሥራት መግባባታቸውን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ.ር) አስታወቁ።
Next articleየወባ በሽታ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱን የደብረማርቆስ ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ።