“ሁላችንም ያጋጠመን ችግር እና መፍትሔ ላይ በግልጽ ተወያይተን ወደ ሥራ መግባት አለብን” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው

38

ባሕር ዳር: ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ”ሠላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሠላም” በሚል መሪ ሃሳብ የሰሜን ጎጃም ዞን እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የመሥሪያ ቤቶች ቡድን መሪዎች ውይይት ተጀምሯል። ውይይቱ በወቅታዊ የሠላም ችግር እና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያተኮረ ነው።

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ባለፉት ወራት ሀገርን አደጋ ላይ የጣለ የሰላም ችግር ተፈጥሮ እንደነበር ጠቅሰው በተደረገው ጥረት የተሻለ ሰላም መገኘቱን ገልጸዋል።

ይህንን ሰላም አጽንቶ በሙሉ አቅም ወደ ልማት ለመግባት የመንግሥት ሠራተኛው ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተወያይቶ አገልግሎት አሰጣጡንም ማሳደግ አስፈላጊ መኾኑን ጠቅሰዋል።

ሰላም የሁሉም ነገር ቅድመ መሠረት ነው። ሰላምን የሚያደፈርሱ ነገሮችን በመፍታት ወደተረጋጋ ሰላም እና የልማት ሥራ ለመግባት ከሠራተኛው ጋር መወያየት ማስፈለጉንም ተናግረዋል።

የተከሰተው ግጭት እና ቀውስን ከዚህ በላይ እንዲቀጥል መፍቀድ ለከፋ ጉዳት መዳረግ ነው፤ ለዚህም ሁላችንም ያጋጠመን ችግር እና መፍትሔ ላይ በግልጽ ተወያይተን ወደ ሥራ መግባት አለብን ነው ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ በኢንተርፖል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው።
Next articleኢትዮጵያ እና ጀርመን በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ እና በግብርና ምርቶች ላይ በጋራ ለመሥራት መግባባታቸውን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ.ር) አስታወቁ።