“ሰላም የመጀመሪያም የመጨረሻም አማራጭ እና የመፍትሔ አካል ሊሆን ይገባል” ግዛቸው ሙሉነህ

75

ደባርቅ: ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱ ወጣቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና በአዋሳኝ ቀበሌዎች የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተካፍለዋል። በውይይቱ ላይ የተገኙት በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሥራ አስፈጻሚ ደረጃ የዋና ሥራ አስፈጻሚው አማካሪ ግዛቸው ሙሉነህ

“ፅንፈኝነት ማኅበራዊ እና ቁሳዊ ሃብቶቻችንን እየበላ ያለ መነቀል ያለበት አደገኛ በሽታ ነው” ብለዋል። አቶ ግዛቸው “ሰላም የሁሉም ነገር የመጀመሪያም የመጨረሻም አማራጭ እና የመፍትሔ አካል ሊሆን ይገባል ብለዋል። የሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ቢምረው ካሳ ሰላም በፀጥታ ኃይሉ ርብርብ ብቻ የሚመጣ አይደለም፤ ሰላም የጋራ ሃብታችን ነው ብለዋል።

በሰላም ውይይቱ የተሳተፉ ነዋሪዎችም የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ እየተካሄዱ ያሉ የሰላም ውይይቶች ወሳኝ ናቸው ብለዋል። በቀጣይም መንግሥትን እና በጫካ ያሉ ወገኖችን ለማቀራረብ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከገጠመን የሰላም ችግር ወጥተን ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥ እና በልማት ሥራዎች ላይ ማተኮር ይገባል” የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን
Next article“ሕዝቡ ለሰላም ያለውን ቁርጠኛነት በተግባር አሳይቶናል” ሹመት ጥላሁን