
ባሕር ዳር: ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሉማሜ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘውን የሰላም መድረክ የአማራ ክልል የልማት ድርጅቶች ዋና ሥራ አስፈፃሚ አበባው ጌቴ፣ የ32ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ደርቤ ሽበሽ እና የምሥራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ የሽዋስ አንዷለም እየመሩት ይገኛሉ።
በመድረኩ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የመንግሥት ሠራተኞች እና የአካባቢው አርሶ አደሮች እየተሳተፉ መሆኑን የምሥራቅ ጎጃም ኮሙኒኬሽን አሳውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!