
ባሕር ዳር: ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደምበጫ ዙሪያ ወረዳ የጨረቃ ከተማ ላይ በወቅታዊ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ሕዝባዊ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው። በምዕራብ ጎጃም ዞን ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ በየጨረቃ ከተማ “ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት ነው በወቅታዊ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ የሚገኘው።
በውይቱ ላይ የደምበጫ ዙሪያ ወረዳን ሰላም ለማረጋገጥ የነዋሪዎች ሚና ትልቅ መኾኑ ነው የተገለጸው፡፡ በመድረኩ በብልጽግና ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፊ ኀላፊ ሙላት ጌታቸውን ጨምሮ የመከላከያ መሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ ሴቶች፣ ወጣቶች እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን ከመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!