የምድረ ገነት ከተማ ነዋሪዎች ሰላምን ሊያረጋግጡ ይችላሉ ባሏቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ፡፡

36

ባሕር ዳር: ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎንደር ዞን የምድረ ገነት ከተማ አሥተዳደር ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር “ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት ከማኅበረሰቡ ጋር መክሯል፡፡ በምድረገነት ከተማ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የሰላም ውይይቱ ተሳታፊዎች ሰላምን ለማረጋገጥ ጠንክረው እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ሰላም የሁሉም ነገር መሠረት እንደኾነ ገልጸው ይህን ሰላም ለማረጋገጥ ከመንግሥት ጋር አብረው ለመሥራት ቁርጠኛ መኾናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በአካባቢያቸው ዳግም የሰላም መደፍረስ እንዳይኖር መተማመን እና በጋራ መሥራት እንደሚያስፈልግም ነው የተናገሩት፡፡ ለዚህ ደግሞ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ ነው ያረጋገጡት፡፡

በሕዝባዊ መድረኩ ላይ የምዕራብ ጎንደር ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አበባው በዛብህ፣ የመከላከያ ሠራዊት መሪዎች እና የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች መገኘታቸውን ከአማራ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበፀጥታ ችግር ምክንያት የተቋረጡ የልማት ሥራዎች ወደ ሥራ እንዲገቡ ወጣቱ ለሰላም እንዲሠራ የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር አሳሰበ፡፡
Next articleየደምበጫ ዙሪያ ወረዳን ሰላም ለማረጋገጥ የነዋሪዎች ሚና ትልቅ መኾኑ ተገለጸ፡፡