
ባሕር ዳር: ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ያዘጋጀችውን ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ኮንፍረንስ ዛሬ በኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፣ የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዱዓለም እና የመሀመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ከሊፋ ሙባረክ (ዶ.ር) ተከፍቷል።
በዚሁ መድርክ ላይ የኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር እና የመሀመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ፈጽመዋል።
ስምምነቱን የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ.ር) እና የመሀመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ከሊፋ ሙባረክ (ዶ.ር) ፈርመውታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!