“በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የሠራናቸው ሥራዎች ተጽዕኗቸው ድንበር ተሻጋሪ ነው” ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ

17

ባሕር ዳር: ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባጋሩት መልእክት “የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ ኢንሼቲቭ፤ ለቀጣናዊ ዘላቂ የዉኃ ሀብት ልማት እመርታ” በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በተጀመረው ዓለም አቀፍ የሀይድሮ ሜት ጉባኤ ላይ ተገኝተናል ብለዋል።

መድረኩ ሀገራችን በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ያስመዘገበቻቸውን አመርቂ ድሎች በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ዕድል ፈጥሮልናል ነው ያሉት፡፡

ይሄን ታሳቢ በማድረግ ላለፉት ስድስት ዓመታት ሀገራችን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን በመቅረጽ እስከ ዛሬ ድረስ 40 ቢልዮን ችግኞች ተክለናል ብለዋል፡፡

እነዚህ የተተከሉ ችግኞች ከከባቢ የአየር ሁኔታ፤ ምግብ ዋስትና እና የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር ለቀጣናው ዘላቂ የዉኃ ሀብት ልማትና አስተዳደር ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡

ይህን እጅግ ጠቃሚ ጉባኤ በማዘጋጀት ረገድ ቁልፍ ሚና ለተወጡት የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሠራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡ ጥረታችሁ የትብብርና የቁርጠኝነት ኃይል ማሳያ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያ ለዘመናት የቆየ የሃይማኖቶች መቻቻልና አብሮ መኖር ያለባት ሀገር ናት” ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
Next articleየሰላም ሚኒስቴር እና የመሀመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት አደረጉ።