
ባሕር ዳር: ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን የመርጦለማርያም ከተማ እና አካባቢው ማኅበረሰብ የአካቢውን ሰላም ለማስጠበቅ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ነው እየመከሩ የሚገኙት፡፡
በምክክሩ የአማራ ሕዝብ ዝክረ ታሪክ ማዕከል ኀላፊ አዲስ በየነ፣ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ሕዝብ ቅሬታ ሰሚ ኀላፊ ካሳሁን አላምሬ እና የ71ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አዱኛ ማሞ ተገኝተዋል።
መድረኩ “ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ሲኾን የመርጦለማሪያም ከተማ እና አካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል። ነዋሪዎቹ የአካባቢያቸውን ሰላም ለማስጠበቅ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ መሥራት የሚጠይቅ እንደኾነ ነው የተናገሩት፡፡
ሰላምን ለማስጠበቅ መግባባት ወሳኝ ጉዳይ መኾኑን ገልጸው ከመንግሥት ጋር ተቀናጅተው ሰላማቸውን ለመጠበቅ እንደሚሠሩ መናገራቸውን ከምሥራቅ ጎጃም ዞን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!