
ባሕር ዳር: ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ)ኢትዮጵያ ያዘጋጀችው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ኮንፈረንስ ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፍቷል።
ይህንን ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ኮንፈረንስ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ፣ የሰላም ሚኒስትሩ ብናልፍ አንዱዓለም እና የመሐመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ዶክተር ከሊፋ ሙባረክ ከፍተውታል።
በኮንፈረንሱ ላይ ከ16 ሀገራት የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶችና የተቋማት መሪዎች እየተሳተፉ ነው።
ኢፕድ እንደዘገበው ኮንፈረንሱ በልዩ ልዩ መርሐ ግብሮች እስከ ነገ እንድሚቀጥል ታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!