
ባሕር ዳር: ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምርት እና ምርታማነትን በመጨመር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ግብርናን ወደ ሜካናይዜሽን እርሻ ማሸጋገር አማራጭ የሌለው ቀዳሚ የግብርና ልማት ተግባር መኾኑን የሰሜን ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኀላፊ መልካሙ አለኸኝ ገልጸዋል።
አቶ መልካሙ አለኽኝ ከግብዓት የድጎማ በጀት በተገኘ ድጋፍ ለአርሶ አደሮች 13 የተሻሻሉ የፈረሰ ጉልበት ያላቸው ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮች ግዥ መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡
ለእርሻ ትራክተሮችም ከ182 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጭ ግዥ መፈጸም ስለመቻሉም ነው ያስገነዘቡት፡፡
የተገዙ የእርሻ ትራክተሮችን በየወረዳው ለአርሶ አደሮቹ ማስረከባቸውን የገለጹት ምክትል መምሪያ ኀላፊው የአርሶ አደሮችን ጉልበት እና ጊዜ ከሚጠይቀው የበሬ እርሻ ጫና ለማላቀቅ ቴክኖሎጂ ላይ መሥራት እንደሚገባም መናገራቸውን ከርእሰ መሥተዳደር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!