
ደብረ ማርቆስ: ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት በደጀን ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የተገኙት የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ኑርልኝ ብርሃኑ የሰላምን ዋጋ በመገንዘብ የባለፈው ችግር እንዳይደገም የሚያደርገውን መንገድ መከተል እና በመተባበር ሰላምን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጅ ቢሮ ኀላፊ ማማሩ አያሌው (ደ.ር) መንግሥት በወሰደው የሰላም ቁርጠኝነት በመከላከያ ሠራዊት፣ በክልሉ የፀጥታ ኀይል እና በሕዝቡ ትብብር የተገኘውን ሰላም ዘላቂነት ለማረጋገጥ የሁሉም ኀላፊነት ሊኾን ይገባል ነው ያሉት።
የሰላም ኮንፈረንሱ ተነጋግሮ ለመግባባት፣ ለተከሰተው የሰላም መደፍረስ ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት እና ሰላምን ለማረጋገጥ በጋራ የሚሠራበት ሊኾን እንደሚገባም አሳስበዋል።
በመድረኩ ከደጀን ከተማ እና ከደጀን ወረዳ የተውጣጡ ነዋሪዎች እና መሪዎች እንዲኹም የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች እየተሳተፉ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!