በመስኖ ልማት ከ4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማምረት አቅዶ እየሠራ መኾኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን አስታወቀ።

22

ደብረ ማርቆስ: ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በዚህ ዓመት በምሥራቅ ጎጃም ዞን በመስኖ ልማት በዘር ከሚሸፈነው 29 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ ከ4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሠራ መኾኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ አበበ መኮንን ተናግረዋል፡፡
በዞኑ ለመስኖ ስንዴ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው ብለዋል ኀላፊው፡፡

በዘር ለመሸፈን ከታቀደው መሬት ውስጥ ከ16 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ስንዴ የሚሸፈን ነው ብለዋል፡፡

ለመጀመሪያው ዙር መስኖ ልማት ከ25 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ መቅረቡንም ተናግረዋል። በዚህ ዓመት የግብዓት አቅርቦት ችግር ለአርሶ አደሮች ፈተና እንደማይሆን ነው የገለጹት፡፡ አርሶ አደሮችም ግብዓትን በአግባቡ እና ለታለመለት አላማ እንዲጠቀሙ አሳስበዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ለአርሶ አደሮች ከተሰራጩት 7 ሺህ የውኃ ማሰራጫ ፓምፖች በተጨማሪ ሌሎች 193 ፓምፖች ለስርጭት ዝግጁ መሆናቸውን መምሪያ ኀላፊው ተናግረዋል፡፡ ይህም ለመስኖ ልማት ውጤታማነት የጎላ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡

አርሶ አደሮች ለመስኖ አውታር ጠረጋ እና ውኃ አሠባሰብ ሥራዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ለበጋ መስኖ ውጤታማነት የበኩላቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበደቡብ ወሎ ዞን ሃርቡ ከተማ የሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው።
Next articleየተገኘውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል በጋራ መሥራት እንደሚያስፈልግ የጋዝጊብላ ወረዳ አሥተዳዳሪ ተናገሩ።