“ተቋማት እና መንግሥት በሰብዕና ግንባታ ላይ ትኩረት አድርገው ሊሠሩ ይገባል” ተድላ ኩታዬ (ዶ.ር )

41

ደብረ ብርሃን: ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በመልካም ሰብዕና የተቀረፀ ትውልድ ለመገንባት ቤተሰብ፣ ማኅበረሰብ እና ተቋማት ያላቸው ሚና ጉልህ መኾኑን በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልቦና ትምህርት ክፍል መምህሩ ተድላ ኩታዬ (ዶ.ር ) ተናግረዋል።

የሰው ልጅ አብሮት የሚወለድ ተፈጥሯዊ እና ደመ ነፍሳዊ የኾነ ፍላጎት፣ ባሕሪ እንዲሁም በሂደት የሚማራቸው ማኅበረሰባዊ የኾኑ ሕጎች በሰብዕና ግንባታ ውስጥ ይንፀባረቃሉ ብለዋል።

እነዚህን ፍላጎቶች በማጣጣም መልካም ሥነ ምግባርን እና ሰብዕናን መላበስ ይቻላል የሚሉት ዶክተር ተድላ የራስን ፍላጎት ከብዙኀኑ ፍላጎት፣ ባሕል፣ ዕምነት እና እሴት ጋር ማጣጣም ተገቢ መኾኑን ተናግረዋል።

ጤናማ ሰብዕና መጀመሪያ የሚጠቅመው ራሱ ግለሰቡን ሲኾን ለማኅበረሰብም ኾነ ለሀገር ያለው ጠቀሜታ ጉልህ እንደኾነ አስገንዝበዋል።

ጤናማ ማኅበረሰብ የሁሉም መሠረት በመኾኑ የሀገር ሰላም እና ልማትን ለማረጋገጥ በቅድሚያ በትውልድ ሰብዕና ግንባታ ላይ ሊሠራ እንደሚገባ አንስተዋል።

ወላጆች፣ ማኅበረሰቡ፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት እና መንግሥት በሰብዕና ግንባታ ላይ ትኩረት አድርገው ሊሠሩ እንደሚገባ ዶክተር ተድላ አስረድተዋል።

ዘጋቢ፦ ሥነ-ጊዮርጊስ ከበደ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በ2017 ዓ.ም በመስኖ 47 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታስቦ ወደ ተግባር ተገብቷል” የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ
Next articleበደቡብ ወሎ ዞን ሃርቡ ከተማ የሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው።