የአረጋውያን ቀን አከባበር የማጠቃለያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው።

76

ባሕር ዳር: ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ሴቶች፣ ህጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስተባባሪነት ሲከበር የቆየው የአረጋውያን ቀን የማጠቃለያ ሥነ ሥርዓት እየተከናወነ ነው።

“ክብር እና ፍቅር ለአረጋውያን” በሚል መሪ መልእክት ሲከበር በሰነበተው መርኃ ግብር የዛሬ ማጠቃለያ ሥነ ሥርዓት በባሕር ዳር ከተማ ለሚገኘው ዝግባ የሕጻናት እና የአረጋውያን መርጃ የበጎ አድራጎት ድርጅት አረጋውያን ማዕድ የማጋራት ተግባር ተከናውኗል። የብርድ ልብስ እና አንሶላ ድጋፍም ተደርጓል።

የማጠቃለያ መርኃ ግብሩም በውይይት እና በምስጋና ዝግጅቶች ይከበራል።

በሥነ ሥርዓቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ እና በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)ን ጨምሮ የክልሉ እና የሲቪክ ማኅበራት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሃሳብ የፀናች እና በምክክር የቀናች ሀገር መገንባት ያስፈልጋል!
Next articleየስንዴ እሴት ሰንሰለት ልማት ፕሮጀክት ስንዴን በማልማት ሂደት የሚገጥሙ ችግሮች እንደሚፈታ ተገለጸ።