
ባሕር ዳር: ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በምህንድስናው ዘርፍ ወጤታማ ስኬቶችን ለማስመዝገብ የዲጂታላይዜሽን ትግበራ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በባሕር ዳር ከተማ የሚገኘውን የልህቀት ዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን የሪፎርም ሥራዎችን መጎብኘታቸውንም ነው የገለጹት፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመለከትናቸው ምቹ የሥራ ከባቢ ግንባታ እና የዲጂታላይዜሽን የሪፎርም ሥራዎች በምህንድስናው ዘርፍ ኮርፖሬሽኑን ወደ ተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ ናቸው ብለዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!