እስከ አሁን የተመዘገቡ ተማሪዎች 31 በመቶ ገደማ መኾናቸውን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡

68

ባሕር ዳር: ጥቅምት 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2017 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና በቀጣይ መደረግ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ከዞን የትምህርት መምሪያ ኀላፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ መኳንንት አደመ ባለፉት አራት ዓመታት የትምህርት ዘርፉ በተለያዩ ምክንያቶች መፈተኑን ገልጸዋል።

ችግሩን ለመሻገር ከማኅበረሰቡ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ውይይቶች ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ መሠራቱን ነው የተናገሩት።

ይሁን እንጅ አሁን ላይ በተደረገው ውይይት መጠን መመዝገብ የሚጠበቀውን ተማሪ መመዝገብ አለመቻሉን ገልጸዋል።

ከ7 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ እስከ አሁን ከቅድመ አንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል የተመዘገቡት 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተማሪዎች ብቻ ናቸው።

አሁን የተመዘገበው የተማሪ ቁጥር ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገበው ያነሰ መኾኑንም አብራርተዋል።

ማንኛውም ለክልሉ የሚያስብ ቡድን ለትምህርት ቅድሚያ እንዲሰጥም ጥሪ አቅርበዋል። የተመዘገበውን ተማሪም ማስተማር ይገባል ነው ያሉት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሀገር የሚያፈርስ ሃሳብ እና የፖለቲካ አካሄድ ሊወገድ እንደሚገባ የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዲያቆን ሸጋው ውቤ ገለጹ።
Next articleየወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ተማሪዎቹን አስመረቀ።