በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ምስጋኑ አርጋ የተመራ ልዑክ በአራተኛው የብሪክስ አስተባባሪዎች ስብሰባ እየተሳተፈ ነው።

30

ባሕር ዳር: ጥቅምት 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አራተኛው የብሪክስ ዋና እና ምክትል አስተባባሪዎች ስብሰባ በሩሲያ ካዛን ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በስብሰባው ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ እና የኢትዮጵያ የብሪክስ ጉዳይ ምክትል አስተባባሪ ምስጋኑ አርጋ የተመራ ልዑክ በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡

በሩስያ የወቅቱ ሊቀመንበርነት እየተመራ ባለው ስብሰባ ላይ ዋና እና ምክትል አስተባባሪዎቹ የካዛን ረቂቅ ስምምነትን እንዲሁም የብሪክስ አጋር ሀገራት አሠራርን ማዘጋጀት ላይ አተኩረው እንደሚሠሩ ይጠበቃል፡፡

16ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባዔ ከጥቅምት 12 እስከ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በሩሲያ ካዛን ከተማ እንደሚካሄድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤትን በመሰብሰብ የማክሮ ኢኮኖሚ እድገት እና ቁልፍ የክዋኔ መስፈሪያዎች የቀረቡበትን የካቢኔ የ100 ቀን የአፈፃፀም ግምገማ አስጀምረዋል።
Next article“የምንገነባቸው ትርክቶች ለጋራ፣ ለአብሮነት እና ለአንድነት የሚጠቅሙ መኾን ይገባቸዋል” ሠልጣኞች