
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤትን በመሰብሰብ የማክሮ ኢኮኖሚ እድገት እና ቁልፍ የክዋኔ መስፈሪያዎች የቀረቡበትን የካቢኔ የ100 ቀን የአፈፃፀም ግምገማ አስጀምረዋል። ግምገማው አለምአቀፋዊ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዝንባሌዎችን እና ፍኖቶችን በመፈተሽ በኢትዮዽያ ላይ የሚኖራቸውን ተፅዕኖ ተመልክቷል።
8.45 በመቶ በተተነበየው የመጪው አመት እድገት የለውጡ አበረታች ውጤቶች አካታች እና ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን የሚያሳዩ፣ የጨመረ የመንግሥት ገቢ እና ኢንቨስትመንት ያስገኙ፣ የመንግሥት ዕዳን የቀነሱ፣በመንግሥት ይዞታ ስር ያሉ ተቋማትን ተወዳዳሪነት የጨመሩ፣ የውጭ ምንዛሪ ያስገኙ፣ የበለጠ ተወዳዳሪነትን የታየበት የፋይናንስ ዘርፍ ያመጡ፣ ምቹ የኢንቬስትመንት ከባቢን የፈጠሩ ብሎም የዘርፍ ምርታማነትን ያሳደጉ ሆነዋል። የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት በተለይም እንደ ማኑፋክቸሪንግ እና ኮንስትራክሽን ባሉ ዘርፎች የተፋጠነ እንደሚሆን ይጠበቃል።