
ባሕር ዳር: ጥቅምት 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የቆየውን የክልሉ መሪዎች ሥልጠና ማጠቃለያን አስመልክተው በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ተከታዩን መልእክት አስተላልፈዋል፦
ከትላንት ታሪካችን በጎዎችን እያደስንና እያስዋብን፣ ህፀፆችን እያረምንና እያስተካከልን፣ በትናንትናው ብቻ ሳንታጠር፤ ዛሬን በአገልጋይነት ስሜትና በታታሪነት፣ በከፍተኛ የትጋት መንፈስ ጠንክረን በመሥራት፤ የልፋትና ድካም ውጤታችን የሚንፀባረቅበት ያማረና የተዋበ ነጋችንን ለመጭው ትውልድ በማውረስ ታሪክ እንሠራለን!
ለዘመናት ጠፍሮ ከያዘን አዙሪት ተላቀን፤ ዕድሎቻችንን ሳናባክን፤ የገጠሙንን ችግሮች እየተጋፈጥን፤ በስኬቶቻችን ሳንዘናጋ ወደ ብልፅግናችን እንገሰግሳለን፡፡
በዚህም ሁለንተናዊ ሉዓላዊነቷ የተረጋገጠ አፍሪካዊት ልዕለ ኃያል ሀገር ለልጆቻችን ለማቆዬት ያገኘነውን መልካም ዕድል ሳናባክን እንጠቀማለን፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!