
አዲስ አበባ:ጥቅምት 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበረ ያዘጋጁት የሴት ስታርታፖች ውድድር የመዝጊያ ፕሮግራም ተካሂዷል። ከመላው የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ 37 ሴት ስታርታፖች የተሳተፉበት ውድድር ዛሬ ሲጠናቀቅ አሸናፊ ለኾኑት 10 ተወዳዳሪዎች ለእያንዳንዳቸው የ100 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ.ር) ሴቶች የሚሳተፉበት ኢኮኖሚ የመለወጥ እድሉ ከፍተኛ መኾኑን ገልጸዋል። በአይሲቲ/ICT/ ኢኖቬሽን ዘርፍ የሕዝቡን ሕይወት ለመቀየር ወጣት እና ሴቶችን ማብቃት ላይ መሥራት አለብን ብለዋል። በዘርፉ ምቹ ኹኔታዎችን ለመፍጠር ደግሞ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሁሉ ፖሊሲ በመቅረጽ እገዛ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።
ሴት ስታርታፖቹ በአይቲ ፓርክ ኢኖቢዝ – ኬ ኢትዮጵያ ማዕከል ውስጥ ላለፉት 10 ቀናት የተለያዩ የክህሎትና የቢዝነስ ሥልጠናዎችን ሲወስዱ መቆየታቸውም ተገልጿል።
ዘጋቢ:- ቤተልሄም ሰለሞን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!