
ባሕር ዳር: ጥቅምት 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እምቦጭን ለባዮ ጋዝ መጠቀም የሚያስችል አዲስ የምርምር ውጤቱን ወደ ተግባር ለማሸጋገር የሚያስችለውን የመስክ ላይ የሙከራ ፕሮጀክት መጀመሩን አስታውቋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ደሴ ጥበበ (ዶ.ር) ዩኒቨርሲቲው እምቦጭን ለባዮ ጋዝ መጠቀም የሚያስችል ምርምር እያካሄደ መኾኑን መግለጻቸውን የኢዜአ ዘገባ አመላክቷል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!