“አብርኾት የትውልዶችን ልቦና በእውቀት ለማብራት የተቋቋመ ነው”

36

ባሕር ዳር: ጥቅምት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት “አብርኾት የትውልዶችን ልቦና በእውቀት ለማብራት የተቋቋመ ነው” ብለዋል። በሕንጻው ምሰሶዎች ጥበብ የሚለው ቃል በ18 የራሳቸው ፊደል ባላቸው ቋንቋዎች ተፅፎ የሚገኘውም ለዚህ ተልዕኮ ያለውን ቁርጠኝነት ለማመላከት ነው ሲሉም ገልጸውታል።

አብርኾት ቤተመፃህፍት በብልሃት ክህሎት የተጎናፀፉ ወጣቶችን የማብቃት ዓላማውን በትጋት በመወጣት ላይ ይገኛልም ነው ያሉት። ዛሬ በአብርኾት ያገኘኋቸው ወጣቶች እንደ ሮቦቲክስ እና የፈጠራ ትግበራ ሥራዎች ላይ ተጠምደው ስላገኘኋቸው አድናቆት እና ማበረታቻ ይገባቸዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መጪው ትውልድ ከኢትዮጰያ የልማት ግቦች ጋር በተናበበ ሁኔታ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በኮዲንግ፣ በሳይበር ሴኩሪቲ እና በመሳሰሉት ዘርፎች ክህሎታቸውን ማጠናከር መቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አፍሪካ እያጋጠሟት ያሉትን ችግሮች የውጭ ኃይሎች እንዲፈቱላት ማማተር አይገባትም” ዳይሬክተር ጄኔራል ሬድዋን ሁሴን
Next article“የኢትዮጵያን ብልጽግና በዘላቂነት ለማረጋገጥ ነገን የሚዋጁ ታዳጊዎችን ማፍራት ላይ በትብብር መሥራት ይገባል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)