“ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ሰላምን ማረጋገጥ አይቻልም” የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ

47

ደባርቅ: ጥቅምት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የደባርቅ ነዋሪዎች በሰላም እና ፀጥታ ጉዳይ ምክክር አድርገዋል። በውይይቱ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል። የሰሜን ጎንደር ዞን ኮማንድፖስት የሥራ ኀላፊዎች እንደገለጹት እንደ ሀገር ሰላም እና አንድነት እንዳይኖር ታሪካዊ የውጭ ጠላቶቻችን ያለ ዕረፍት እየሠሩ ነው፤

እየተከሰቱ ያሉ የእርስ በእርስ ግጭቶችም የዚህ ማሳያ ናቸው ብለዋል። ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ሰላምን ማረጋገጥ አይቻልም ያሉት የሥራ ኀላፊዎቹ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ለሰላም ዘብ እንዲቆም ጥሪ አስተላልፈዋል። በክልሉ የተከሰተው ግጭት ሕዝብን ለከፋ ችግር እና ጉስቁልና ዳርጎታል ሲሉ የሰሜን ጎንደር ዞን አሥተዳዳሪ ዲያቆን ሸጋው ውቤ ተናግረዋል።

በፀጥታ ኃይሉ ጥረት ብቻ ለውጥ ማምጣት እንደማይቻልም ነው ዋና አስተዳዳሪው ያስገነዘቡት። በመኾኑም ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ለሰላም ዋጋ ሰጥቶ መሥራት አለበት ብለዋል። ከተለያዩ ቀበሌዎች የተውጣጡ የፀጥታ መዋቅር አባላት የወንድማማቾች ግጭት ትርፉ አስከፊ ሞት በመኾኑ ሰላም አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው ብለዋል።

ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የሰላም ዋጋ በምንም እንደማይተመን ተረድቶ ቅድሚያ ለሰላም ዋጋ እንዲሰጥም አሳስበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በክልሉ የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ ለመከላከል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው” ግብርና ቢሮ
Next article“የወል ትርክትን በመገንባት ጊዜያዊ ፈተናዎችን መሻገርና ሀገራዊ ለውጡን ለማጽናት ዜጎች በጋራ ሊቆሙ ይገባል” አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ