
ባሕር ዳር: ጥቅምት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የትብብር እና አጋርነት ዳይሬክተር አንሙት ታደለ (ዶ.ር) እንዳሉት ኮሌጁ ከ “ችልድረንስ ሰርጀሪ ኢንተርናሽናል” ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በተፈጥሮ የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ላለባቸው ሕፃናት ነፃ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ይሰጣል።
ሕክምናው ከጥቅምት 9/2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 15 /2017 ዓ.ም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እንደሚሰጥ ነው የተናገሩት። ችግሩ ያለባቸው ሕጻናት ሕክምናውን እንዲያገኙ ሁሉም ኀላፊነቱን እንዲወጣም አሳስበዋል። ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ከዚህ በፊትም ከኮሌጁ ጋር በመተባበር ሕክምናውን መስጠቱን ነው ያስታወቀው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
