“75ኛውን ዓለም አቀፍ የጠፈር ተመራማሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያን በዘርፉ ቀዳሚ እና ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን ለመፍጠር እንጠቀምበታለን” ይሽሩን ዓለማየሁ (ዶ.ር)

45

ባሕር ዳር: ጥቅምት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ “ኀላፊነት የተሞላበት የሕዋ አጠቃቀም ለዘላቂነት” በሚል መሪ መልዕክት በጣሊያን እየተካሄደ በሚገኘው 75ኛው ዓለም አቀፍ የጠፈር ተመራማሪዎች ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው። በጉባኤው ከ11 ሺህ በላይ የዘርፉ ምሁራን፣ የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም፣ የአውሮፓ የሕዋ ኤጀንሲን ጨምሮ ከመላው ዓለም የተውጣጡ የጠፈር ተመራማሪዎች ተሳትፈዋል።

በጉባኤው የተሳተፉት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን ዓለማየሁ (ዶ.ር) መድረኩ ለኢትዮጵያ የህዋ ፕሮግራም ዓለም አቀፍ አጋሮችን ለማግኘት ጠቀሜታ እንዳለው ነው የገለጹት፡፡ ኢትዮጵያን በዘርፉ ቀዳሚ እና ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን ለመፍጠር እንጠቀምበታለንም ብለዋል።

መድረኩ በትምህርት ዘርፍም ኾነ በኢንዱስትሪ ደረጃ በሕዋ ላይ ያሉ አዳዲስ ክስተቶችን እና የዘርፉ ዕድገት ያለበትን ደረጃ ሁሉም ሰው እንዲያውቅ ለማድረግ የሚዘጋጅ ነው።

በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎች በአንድ መድረክ እንዲገናኙ እና በጋራ መሥራት የሚችሉባቸውን አማራጮች እንዲያዩም ለማስቻል የሚዘጋጅ መኾኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleባዮኒክ ዕይታ
Next articleከ80 ሺህ ቶን በላይ ደረቅ ቆሻሻን ወደ ሃብት መቀየር መቻሉን የአዲስ አበባ ጽዳት አሥተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ።