የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ያልፈረሙ ሀገራት እንዲፈርሙ ጥሪ ቀረበ።

48

ባሕር ዳር: ጥቅምት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ለቻይና ግሎባል ቴሌቪዥን ጣቢያ ሲ.ጂ.ቲ.ኤን በሰጡት መረጃ የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በተፋሰሱ አባል ሀገራት መካከል የልማት ትብብር የሚያጠናክር መኾኑን ገልጸዋል።

አምባሳደር ነብያት ይህን ፍትሐዊ እና እኩል ተጠቃሚነትን የሚያሰፍነውን የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ያልፈረሙ ሀገራት እንዲፈርሙም ጥሪ አቅርበዋል። ቃል አቀባዩ ስምምነቱ ወደ ተግባር መግባቱ በናይል ወንዝ ተፋሰስ የውኃ ዲፕሎማሲ ጉዞ ታሪካዊ ስኬት መኾኑንም አንስተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየትውልዱ መልካም ሥነ ምግባር እንዴት ይመለስ?
Next articleበየወቅቱ በሚፈጠሩ ተፅዕኖዎች የማይናወጡ ተቋማትን መገንባት መቻል የተረጋጋ ሀገርን ለመፍጠር ቁልፍ መንገድ መኾኑ ተገለጸ፡፡