
ባሕር ዳር: ጥቅምት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት የጎላ ሚና የሚኖረው የካፒታል ገበያ በአንጋፋው የኢትዮ ቴሌኮም የ10 በመቶ የአክስዮን ሽያጭ ሥራው መጀመሩን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት የካፒታል ገበያ በሀገራችን ኢንቨስትመንት እና ቁጠባን ከማሳደጉ ባሻገር አካታች የፋይናንስ ዘርፍን በማሳደጉ ረገድ ትልቅ ሚናን ይጫወታል፡፡
የ130 ዓመታት ዕድሜ ባለፀጋው ኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክስዮን ድርሻውን በሽያጭ ለሕዝብ ማቅረቡ ትልቅ ስኬት ስለመኾኑም አንስተዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የካፒታል ገበያው ጅማሮ ኢትዮጵያን ወደ ተሳለጠ እና ዘመናዊ የአክስዮን ገበያ ሥርዓት የሚያስገባት እና የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድግ ድንቅ ክዋኔ ነው፤ ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አለን!” ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
