
ደባርቅ: ጥቅምት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ ከመንግሥት ሠራተኞች እና አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።
የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዲያቆን ሸጋው ውቤ በውይይቱ ተገኝተው በዚህ ወቅት በተለይም ክልላዊ ላይ የፀጥታ ችግር እንዳለ አብራርተዋል፡፡ ለፀጥታ ችግሩ ትልቁ ምክንያት ታሪካዊ የሀገሪቱ ጠላቶች እጅ መርዘም እንደኾነ ተናግረዋል።
የቀጣናውን ሰላም እና ደኅንነት ለመጠበቅ መንግሥት በሚወስደው ማንኛውም የሕግ ማስከበር ተግባር የወረዳው የመንግሥት ሠራተኞች እና መሪዎች ከመንግሥት ጎን እንዲሰለፉም ጠይቀዋል።
የሕግ የበላይነትን ለማስፈን የጸጥታ መዋቅሩ ሕግ የማስከበር ዘመቻ ላይ በመኾኑ ማኅበረሰቡ፣ የመንግሥት ሠራተኞች እና መሪዎች ከጎናቸው እንዲሰለፉ በውይቱ የተገኙ የመከላከያ አዛዦችም መልዕክት አስተላልፈዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በውይይቱ ደስተኛ መኾናቸውን እና ከውይይቱ ብዙ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይ ጊዜያትም የክልሉ ሰላም እና ደኅንነት እንዲጠበቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!