
ባሕር ዳር: ጥቅምት 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕርዳር ዳር ከተማ ግሽ አባይ ክፍለ ከተማ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 3 ሺህ ሊትር ነዳጅ ተያዘ፡፡
ነዳጁ በሕገ-ወጥ መንገድ ከማደያዎች በሌሊት ተቀድቶ ሲወጣ በተደረገ ክትትል ከነተጠርጣሪዎቹ እጅ ከፍንጅ መያዙን የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
10 በርሚል እና ከ50 በላይ ባለሁለት ሊትር ቤንዚን በክትትል ከተጠርጣሪዎቹ እጅ እንደተገኘም የከተማዋ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!