
ባሕር ዳር: ጥቅምት 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከአውሮፓ ኅብረት ዓለም አቀፍ የትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የሁለትዮሽ ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ፕሬዚዳንት ታዬ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል፡፡
የአውሮፓ ኅብረትን አጋርነት በይበልጥ ማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም የሚከናወኑ ሥራዎች ተጠናክረው በሚቀጥሉበት ሁኔታ ላይ መስማማታቸው ተገልጿል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!