149ኛው ዓለም አቀፉ ፓርላማ በተላያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል፡፡

28

ባሕር ዳር: ጥቅምት 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የተመራ ልዑክ በዓለም አቀፉ የፓርላማ ኅብረት ሥብሠባ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡ በአፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ከጥቅምት 13 እስከ 17/2024 ድረስ በጄኔቫ እየተካሄደ በሚገኘው 149ኛው የዓለም አቀፉ የፖርላማ ኅብረት ሥብሠባ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።

ኅብረቱ በዚህ ጉባኤው በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን፣ ሰላም እና ፀጥታን በማስፈን ዙሪያ እና የዴሞክራሲያዊ አሥተዳደርን ማጎልበት በሚሉ ዋና ዋና ርዕሶች ዙሪያ በመምከር ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል። በተጨማሪም ሀገራት የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች መፍትሄ ለማመላከት እና በፓርላማ ደረጃ ሊተገበሩ የሚችሉ የትብብር መፍትሄዎችን ለመፈተሽ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ዙሪያም ይመክራል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ተሳትፎ ሀገሪቱ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር ትብብሯን ይበልጥ ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይም በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመልክቷል፡፡ የልዑካን ቡድኑ በቆይታው በዘርፉ የሀገራችንን ልምድ በተመለከተ ተሞክሮውን እንደሚያካፍልም እንደሚጠበቅ ተጠቅሷል።

የዓለም አቀፉ የፖርላማ ኅብረት ጉባኤ በዓለም ዙሪያ ላሉ የፓርላማ አባላት ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን ለመወያየት እና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር መድረክ መኾኑ ይታወቃል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበግልጽ ችሎት በመዳኘት ፍትሕን የማስፈን ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ።
Next articleየመንግሥት ሠራተኞች ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት እና ሰላም እንዲሰፍን ለሚደረገው የሕግ ማስከበር ጥረት ከመንግሥት ጎን እንደሚቆሙ አስታወቁ።