
ባሕር ዳር: ጥቅምት 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችን እና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ በወልድያ ከተማ አሥተዳደር ተከብሯል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ17ኛ ጊዜ በሚከበረው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ላይ የወልድያ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አለማየሁ ነጋ በዓሉን ስናከብር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ከፍታ ታሳቢ በማድረግ ነው ብለዋል።
ሰንደቅ ዓላማ የኅብረ ብሔራዊነታችን መገለጫ በመኾኑ የሰንደቅ ዓላማን ክብር ለትውልድ ማሻገር እንደሚገባም አሣሥበዋል።
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ፍትሕ መምሪያ ኃላፊ ሰማዬ ፈለቀ የሰንደቅ ዓላማን ክብር ሁላችንም በየሴክተር ተቋሞቻችን የማፅናት ኃላፊነት አለብን ነው ያሉት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!