
አዲስ አበባ: ጥቅምት 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ)“ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችን እና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ መልዕክት የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተከብሯል።
በመርሐ ግብሩ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ትርጉም ባለው መንገድ ለሀገራዊ አንድነት በመትጋት ሊከበር ይገባል ብለዋል።
“ሰንደቃችን የመሥዋዕትነት፣ የነፃነት፣ የሉዓላዊነታችን መገለጫ እና አርማችን ነው” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።
ጊዜው ከመቸውም በላይ አንድነታችንን የምናጸናበት እና ኢትዮጵያን መካከለኛ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት ጋር እንድትሰለፍ የምናደርግበት ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፡- ራሄል ደምሰው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!