
ባሕር ዳር: ጥቅምት 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በዞኑ በ2016 /2017 የምርት ዘመን 539 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች በዘር መሸፈን መቻሉን የደቡብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ አስታውቋል፡፡ በምርት ዘመኑ በዘር ከተሸፈነው መሬት 19 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅም ተገልጿል፡፡
መምሪያው ለኢንዱስትሪ ግብዓት፣ ለምግብ እና ለውጭ ገበያ የሚውሉ ሰብሎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ማምረቱን ገልጾ በተለይም ለውጭ ገበያ እና ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚቀርቡ ምርቶችን በስፋት እየተመረተ ነው ተብሏል፡፡ በዚህ ዓመት በሰብል ከተሸፈነው 539 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ 28 ሺህ 678 ሄክታር የሚኾነው መሬት በቦሎቄ፣ በሰሊጥ እና በማሾ ምርት መሸፈኑንም መምሪያው አሳውቋል፡፡
ምርቶቹ ጥራታቸው ለውጭ ሀገር ገበያ ተመራጭ እንዲያደርጋቸው ሰብሉ እንደ ደረሰ በትክክለኛው ወቅት ጎርፍ እንዳይገባበት እና ዝናብ እንዳያስገባ በማድረግ እንዲከመር ለአርሶ አደሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እየተሰራ እንደሆነም ተነግሯል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!