“ብሔራዊ ሰንደቃችንን ማክበር ማለት ለሀገራቸው ሲሉ ለተዋደቁ ጀግኖች ክብር መስጠት ነው” አቶ አደም ፋራህ

30

ባሕር ዳር: ጥቅምት 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኀላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የሰንደቅ አላማ ቀን በፓርቲው ቅጥር ግቢ ሲከበር ለጀግኖች ተገቢውን ክብር መስጠት ይገባል ብለዋል።
ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ክብረ በዓል ማለት ኢትዮጵያን ክብር በዓለም አቀፍ አደባባይ ከፍ ላደረጉ ተገቢውን ክብር መስጠት መሆኑን አስረድተዋል።

በዓሉ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የሚከበሩበት ነው ያሉት አቶ አደም ፋራህ ከቀኑ ባለፈ ማንኛውም ዜጋ በተሰማራበት ሙያ በመትጋት ሰንደቃችንን ከፍ ማድረግ ይገባዋል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ዘገባው የኢፕድ ነው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሰንደቅ ዓላማችን ኅብረብሔራዊ አንድነታችን አጣምሮ የያዘ የማንነታችን የጋራ ምልክት ነው” ርእሰ መሥተዳድር
Next articleከሰብል ልማት ከ19 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የደቡብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ፡፡