
ባሕር ዳር: ጥቅምት 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር ምሽት 1፡00 ሰዓት ላይ በአቢጃን ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
ለዚህም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አስቀድሞ ወደ ኮትዲቯር አቢጃን የተጓዘ ሲሆን ለዛሬው ጨዋታ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ ተጠቁሟል፡፡
በጨዋታው አማካዩ ቢኒያም በላይ በጉዳት ከመጨረሻዎቹ ልምምድ ውጭ መሆኑ ሲገለጽ÷ሌሎች ተጫዋቾች በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና ለጨዋታው ዝግጁ መሆናቸውን ፌደሬሽኑ አስታውቋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!