በባሕር ዳር የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ለቱሪስቶች ምቹ ከተሞች ግንባታ ማረጋገጫ መኾናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ገለጹ።

51

ባሕር ዳር: ጥቅምት 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ “በውቢቷ ባሕር ዳር የተገነቡ መናፈሻዎችን እንዲሁም ግዙፉንና አስደማሚውን የአባይ ድልድይ ጎብኝተናል” ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች እጅግ ውብ እና ማራኪ መኾናቸውን አስታውቀዋል።

ለሕዝባችን እንዲሁም ከሩቅም ከቅርብም ለሚመጡ ቱሪስቶች ማረፊያና መዝናኛነት ምቹ የሆኑ ከተሞችን ለመገንባት እየሠራን መሆኑን ማረጋገጫ አሻራዎች መኾናቸውን ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበወሎ ዩኒቨርሲቲ የሚሠሩ ምርምሮች ለፈጠራ ትልቅ አቅም መሆናቸውን ዩኒቨርሲቲው ገለጸ።
Next articleየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት ከጊኒ አቻው ጋር ይጫወታል።