“ከ242 ሺህ በላይ ዜጎች የኮደርስ ሥልጠና እየወሰዱ ነው” የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

24

ባሕር ዳር: ጥቅምት 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ሰላማዊት ካሳ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የወጣቶችን ዓለም አቀፍ የደረጃ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የ5 ሚሊዮን ኮደሮች መርሐ ግብር ተግባራዊ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትር ድኤታ ሰላማዊት ካሳ መርሐ ግብሩ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ 242 ሺህ በላይ ዜጎች ሥልጠና እየወሰዱ መኾኑን ነው ያስገነዘቡት፡፡ ከዚህ ውስጥ ከ81 ሺህ በላይ በመሠረታዊ ፕሮግራሚንግ፣ ከ78 ሺህ በላይ በመሠረታዊ የመረጃ ትንተና፣ ከ82 ሺህ በላይ የሚኾኑት ደግሞ መሠረታዊ የአንድሮይድ አፕሊኬሽን ላይ ሥልጠና እየወሰዱ መኾኑን ገልጸዋል፡፡

ሥልጠናውን በየትኛውም ዘርፍ ላይ የሚገኝ ዜጋ በማንኛውም ቦታ ኾኖ በይነ መረብ ላይ በነጻ በመመዝገብ መከታተል እንደሚቻል ነው ሚኒስትር ድኤታ ሰላማዊት ካሳ ያብራሩት፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ሰርቲፊኬት የሚሰጥበት እንደኾነም አብራርተዋል፡፡ የመመዝገቢያ ሊንኩንም በመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ገጽ ላይ ማግኘት ይቻላል ነው ያሉት ሚኒስትር ድኤታ ሰላማዊት ካሳ፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የከንቲባ ችሎት እና አሚኮ አደባባይ የቴሌቪዥን ፕሮግራም የሕዝብን ጥያቄ እያመላከቱ ነው” አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)
Next articleአረጋውያን ለሀገራቸው የከፈሉትን ውለታ የሚመጥን ድጋፍና እንክብካቤ ሊደረግላቸው እንደሚገባ የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር አሳሰበ።