“ከረሃብ ነጻ የኾነ ዓለም፣ የሚል መርሐ ግብር በጥቅምት ወር በኢትዮጵያ ይካሄዳል” የመንግሥት ኮሙኒዩኬሽን

19

ባሕር ዳር: ጥቅምት 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) መርሐ ግብሩ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፖሊሲዎች የሚቀረጹበት፣ አዳዲስ ሃሳቦች የሚንሸራሸሩበት ይሆናል ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒዩኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ተናግረዋል። በመርኃ ግብሩ ከተለያዩ ዓለማት የመጡ ከ1 ሺህ 500 በላይ እንግዶች ይሳተፉበታል ተብሏል።

መድረኩ ለሦስት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ረሃብን ለመዋጋት የተደረጉ ጥናቶች ይፋ ይደረግበታልም ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታዋ። በመርሐ ግብሩ ከ30 በላይ ዓለም አቀፍ ተቋማት ይሳተፋሉ ።

ኢትዮጵያ መድረኩን በግብርናዉ ዘርፍ እያከናወነች የሚገኘዉን ሥራ ታሳይበታለች፤ የቱሪዝም ሃብቶቿን ታስተዋዉቅበታለች ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለሀገራዊ ሉዓላዊነት መረጋገጥ አይበገሬ ሀገር አቀፍ የሳይበር ደኅንነት አቅምን ማጎልበት እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር አስታወቀ።
Next article“ከ400 ሺህ በላይ ቡክሌቶችን በማሳተም ለዜጎች ተደራሽ ተደርጓል” የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት