
ባሕር ዳር: ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከለሊቱ 9 ሰዓት ጀምሮ በነበረው ከፍተኛ ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት አብዛኞቹ ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ የነበሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሊያርፉ ባለመቻላቸው በአቅራቢያ ወደሚገኙ አማራጭ ኤርፖርቶች ተመልሰው እንዲያርፉ ተገደዋል ብሏል።
አየር መንገዱ እንዳስታወቀው የአየር ሁኔታ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም-አቀፍ የጠዋት በረራዎቻችን ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል። እንደተለመደው የመንገደኞቻችን ደኅንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው ነው ብሏል አየር መንገዱ። ከዚህ ጋር ተያይዞ በተሳፋሪዎቻችን የጉዞ ዕቅዶች ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ መስተጓጉሎችን ለመቅረፍ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረግን እንገኛለን ብሏል።
በዚህ አጋጣሚ መንገደኞቻችን ላጋጠማቸው መጉላላት ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን ብሏል የኢትዮጵያ አየር መንገድ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!