
ባሕር ዳር: ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ለሚከበሩት ለሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በዓላት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
የርእሰ መሥተዳድሩ የእንኳን አደረሳችሁ ሙሉ መልእክት እንደሚከተለው ቀርቧል፦
እንኳን ለሻደይ አሸንድየ እና ሶለል በዓል አደረሳችሁ!
በክልላችን በተለይም በዋግ ኽምራ፣ ሰሜን ወሎ እና ሌሎች አከባቢዎች ከነሐሴ ወር መጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ የሚከበረው ሻደይ፣ አሸንድየ እና ሶለል በልጃገረዶች እና ወጣቶች በባሕላዊ ጭፈራ እና በሃይማኖታዊ ክዋኔዎች የሚከበር ዘመን ተሻጋሪ እና ብዙ ዓመታትን አብሮን የኖረ የሕዝብ በዓል ነው፡፡
የበዓሉ አከባባር መሠረቱ ሃይማኖታዊ መነሻ እንዳለው እና ከነሐሴ 01 እስከ 15 ከሚከናወነው የፍልሰታ ጾም ጋር እና ከቅድስት ድንግል ማርያም ትንሳኤ በዓል ጋር የተገናኘ እንደኾነ ሊቃውንቱ ያስረዳሉ፡፡
ከሃይማኖታዊ አከባበሩ በተጓዳኝም ባሕላዊ መስተጋብር ይሚያብብበት እና አብሮነት የሚደምቅበት፣ የክረምቱን ልምላሜ ያበቀላቸውን እጽዋት በመጠቀም የባሕላዊ ጨፍራ እና አብሮነት ይበልጥ የሚዳብርበት እንዲሁም ወደ አዲስ ዓመት እና መስከረም የብረሃን ወር መሻገሪያ የኾነ የተስፋ እና ደስታ ማብሰሪያ በዓል ነው፡፡
በዓሉን ስናከብር ሕዝባችን ለዘመናት የገነባነውን እሴት በማክበር እና በማሳደግ ከትውልድ ትውልድ በድምቀት እንዲሸጋገር መሥራት ይኖርብናል፡፡
ከማይዳሰሱት ቅረሶች አንዱ የኾነው የሻደይ አሸንድየ እና ሶለል በዓል በቀጣይነት የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ጎብኝዎችን መሳብ አንዲንዲችል፣ ገጽታ መገንቢያ እና ሃብት መፍጠሪያ ኾኖም እንዲያገለግል በጋራ የምንሠራ ይሆናል፡፡
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፤ መልካም በዓል ይሁንላችሁ !
ወዝ ሻደይዙ በሊዝ ችጝዘት
ሻደይዙ በል ብላ ክልል ቺተቺተቊ ጅውንጢዝ ቺተዝም ቊሽ ወይ ኽምረ ብሔረ እቅ ጭሰጭሰኒዝ እብለውትዝ ኪብርሸው በል የጝ፡፡ በልድ እቊንዙ ናፅነይ ቓሊሽተውዝመ ኪብርሸው፣ እኒዝጘም ኪብርኪብርሸነውዝመ ከቨከቭሽተነዊስ ዲቈውዝ ለወንትዝ ሰራሸነውዙ ዲዝጝትድ ጉልምድ ቓሊሽተው በል የጝ፡፡
በልድ ኪብርሻንድ ጅውነይዙ ባኽልዝመ እሴትድ ጉልምድ እትለውዝመ እቀ ህብርድ እቊንዝ ፅይ ፅበው ቀሰው ቓለዝመ እትለድ እኒዝጘም ፅይ ፅበው ክብርድ አደባባይል ቓሊሰው በል የጝ፡፡ በልድ ኹሪስ ኹሪዝጎ ዲቈዲቁሽታጙ ተረው በል የጝ፡፡ እኒን በልድ ኻይን ዊንዘነውዝመ ቀሰው እሴተንድ ላጥ ጅውንጢዝጎ ፈራቓንስ ሰራሸነው ተሚሰኩ፡፡ እጉር ይና አቅሊስ ችጝን ዊንዝነው እን ቀሰው ባኽልዝመ እሴትድ ኻይን ዊንዝነዊዝጘድቅ ላጥ ሰበኒዝም ደግምነጘድ ኻደረ የኩን፡፡
ወዝ ሻደይዙ በሊዝ ችጝዘት
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!