“የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራ ለሀገራችን የእድገት ጉዞ ወሳኝ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ

15

ባሕር ዳር: ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የብሔራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ሶስተኛ መደበኛ ስብሰባውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በተገኙበት አካሂዷል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስብሰባው ተገኝተው የምክር ቤቱን አጠቃላይ የሥራ ክንውን እና የ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ትግበራ አፈጻጸም ገምግመዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት የIT ፓርክን በተመለከተ በተሰጡ ሥራዎች ላይ የክንውን ሪፖርትን የገመገሙ ሲሆን የብሔራዊ ዲጂታል የመንግሥት ስትራቴጂ ቀርቦ በምክር ቤቱ አባላት ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ “የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራ ለሀገራችን የእድገት ጊዞ ወሳኝ ነው” ሲሉም አስገንዝበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሻደይ መቼ እና እንዴት ተጀመረ?
Next articleበ2017 በጀት ዓመት 200 ሺህ የሚጠጉ ወጣቶችን በኮደርስ ኦንላይን ሥልጠና ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑ ተገለጸ፡፡