በኤሌክትሪክ ምሰሶዎች ላይ የሚደርሰውን ሥርቆት በመከላከል ረገድ ኅብረተሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ ተጠየቀ፡፡

12

አዲስ አበባ: ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቶል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በ2016 ዓ.ም በተለያዩ ዘርፎች የተሠሩ ሥራዎች ውጤት እንደተመዘገበባቸው ገልጸዋል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት 19 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 20 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን በጠንካራ ጎን አንስተዋል፡፡ በኃይል አቅርቦት ዙሪያ የምሥራቅ አፍሪካ የኃይል ቋት ለመኾን እየተሠራ ስለመኾኑም ኢንጂነር አሸብር ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በ2016 በጀት ዓመት ያጋጠመው የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች ሥርቆት ከፍተኛ ውድመት እንዳስከተልም ተገልጾል፡፡ በዚኽም ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ መድረሱ ነው የተገለጸው።

በሀገሪቱ ከ50 በመቶ በላይ ዜጎች የኃይል ተጠቃሚ አለመኾናቸውን ያስታወሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው በሚሠሩ ሥራዎች ላይ የሚፈጸሙ ውድመቶችን እና ሥርቆቶችን በመከላከል ረገድ ማኅበረሰቡ ችግሩን በጋራ ለመቅረፍ ሊታገል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዘጋቢ፦ ደረጀ አምባው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአዲስ አበባ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ በተለያዩ ደረጃዎች እና የሙያ ዘርፎች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።
Next articleየዊንዶውስ 11 ዝማኔ