የአዲስ አበባ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ በተለያዩ ደረጃዎች እና የሙያ ዘርፎች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

18

አዲስ አበባ: ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአዲስ አበባ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ በስሩ በሚገኙ የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች በተለያዩ ደረጃዎች እና የሙያ ዘርፎች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል። በተማሪዎቹ የምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ አዲስ አበባ ከተማ ከለውጡ ወዲህ ገጽታዋ እየተቀየረ እና የቱሪስት መስህብ እየኾነች ስለመምጣቷ ተናግረዋል።

ተመራቂዎችም ከተማዋን በማስዋብ ሥራ ተሳታፊ ሊኾኑ እንደሚገባም ጠቁመዋል። ከንቲባዋ ጨምረውም ተመራቂዎች በተማሩት ሙያ እና ክህሎት ራሳቸውን ቀይረው የሌሎችን ሕይዎት እንዲቀይሩም የአደራ መልእክት አስተላልፈዋል።

ተመራቂዎቹ በበኩላቸው በስልጠና ቆይታቸው እውቀት መሸመታቸውን አንስተው የተጣለባቸውን ሃላፊነት በተግባር እንደሚለውጡ ተናግረዋል።

ዘጋቢ፦ አፈወርቅ አበዶም

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየቅድስት ማርያም የእርገት (ሻደይ) በዓል በሰላም እና በፍቅር እንዲከበር ብጹዕ አቡነ በርናባስ አሳሰቡ።
Next articleበኤሌክትሪክ ምሰሶዎች ላይ የሚደርሰውን ሥርቆት በመከላከል ረገድ ኅብረተሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ ተጠየቀ፡፡